ፓርክላንድ ኮሌጅ አርባምንጭ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ1ሺ በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ።

06 September 2025

ፓርክላንድ ኮሌጅ አርባምንጭ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ1ሺ በላይ ተማሪዎችን አስመረቀ። በምረቃ ሥነ ሥርዓቱ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የፓርክ ላንድ ኮሌጅ ባለቤትና ፕሬዝዳንት ዕጩ ዶ/ር ቴዎድሮስ ፋንታዬ ትምህርት የሁሉ ነገር መሠረት እንደሆነና በህብረተሰቡ ውስጥ የሚፈጠሩ ችግሮችን ለመፍታት ብሎም የአካባቢን፤ የሃገርን እንዲሁም የአለማችንን ነባራዊ ሁኔታ የሚቀያይር ቁልፍ መሳሪያ መሆኑን ገልጸው።

ኮሌጁ በተለያዩ የትምህርትመስኮች ለመጀመሪያ ዙር ከደረጃ 1 እስከ 4 ያሰለጠናቸውን ከ1ሺህ በላይ ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት ማስመረቁን ተናግረዋል። ኮሌጁ በ2012 ዓ.ም ከክልሉ ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ቢሮ በተለያዩ የስልጠና መስኮች የምዝገባ ፈቃድ በማግኘት በአርባምንጭ ከተማ ስራዉን መጀመሩ ተጠቁሟል።

በተጨማሪም በሀገር አቀፍ ብሎም በክልሉ መንግስት የወጡ ህጎችንና ፖሊሲዎችን መሰረት በማድረግ በትምህርት፣ በጥናታዊ ፅሁፍ እና በማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎት አምዶችን አዋህዶ ለህብረተሰቡ ተደራሽ እያደረገ የሚገኝ ነዉ ተቋም መሆኑ ተገልጿል። ኮሌጁ ከደረጃ 1 እስከ 4 በዲፕሎማ መርሃግብሮች በአካዉንቲንግ፣ ሂዉማን ሪሶርስ ማኔጅመንት ማርኬቲንግ፣ ሴክሬታሪያል ሳይንስ፣ ሀርድዌርና ኔትዎርኪንግ ሰርቪስ፣ ዳታቤዝ አድሚኒስትሬሽን እና ላይብሬሪ ሳይንስ ዘርፎች በመደበኛዉ፣ በማታና በሳምንቱ መጨረሻ ስልጠና እየሰጠ እንደሚገኝ ጠቁመው።

በቀጣዩ የትምህርት ዘመንም በአዲስ መልክ የአካባቢን ፀጋ መሰረት በማድረግ በኢፌዴሪ ስራ እና ክህሎት ሚኒስቴር የተቀመጠ አቅጣጫ መሰረት በማድረግ። በሾርት ተርም ስልጠናዎችም እንግሊዘኛ ቋንቋ፣ መሰረታዊ የኮምፒዉተር ክህሎት፣ ፒስትሪ አካዉንቲንግ፣ እና የመሳሰሉ ስልጠናዎች ከ3 ወር እስከ 1ዓመት በመስጠት ላይ እንደሚገኝም አብራርተዋል። ከመማር ማስተማር አምድ በተጨማሪ በሃገር አቀፍ፣ በክልል ብሎም በዞን ደረጃ የሚደረጉ የማህበረሰብ አቀፍ አገልግሎቶች በሰፊዉ እየተሳተፈ እንደሚገኝም ጠቁመዋል። በትምህርታቸው የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ኮሌጁ የትምህርትና የሥራ ዕድል እንደፈጠረላቸው ተገልጿል።

የዕለቱ የክብር እንግዳ አቶ ጣሰው ከበደ የጋሞ ዞን የካቢኔ ጉዳዮች አማካሪና የአስተዳደር ተወካይ በፕሮግራሙ ተገኝተው ለተመራቂ ተማሪዎች የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ትምህርት ለሰው ልጆች የማያቋርጥ የህይወት ጎዳና ነው ያሉት አቶ ጣሰው ተመራቂ ተማሪዎች ጥረታቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ በትጋት መሥራት እንዳለባቸው አደራ ብለዋል። ተማሪዎች በኮሌጅ ቆይታቸው የቀሰሙትን እውቀት ህብረተሰቡን በታማኝነትና ጥሩ ስነ-ምግባርን በመላበስ በማገልገል የሚጠበቅባቸውን ኃላፊነት መወጣት እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

የጋሞ ዞን ሙና ቴክኒክ ትምህርትና ሥልጠና መምሪያ ኃላፊ አቶ ወንድሙ ኡቶ የቴክኒክና ሙያ ተቋም የተለያዩ ስልጠናዎችን ተደራሽነትና ፍትሃዊነት በማሳደግ ቴክኖሎጂን በማስፋፋት የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት በማሳደግ የሀገርን ሁለንተናዊ ዕድገት እውን ለማድረግ የሰለጠነ ዜጋና የበቃ የሰው ኃይል ቁልፍ መሳሪያ መሆኑን ጠቁመው። የትምህርትና ስልጠና ጥራት የአንድ ተቋም ብቻ ሳይሆን የሁሉም ርብርብ የሚፈልግ በመሆኑ የአከባቢን ፀጋ የኑሮ ሁኔታ ታሳቢ በማድረግ በቅንጅት ልንሰራ ይገባል ብለዋል።